Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ባቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው ከተወያየ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ሁለቱ ቡድኖች በሃገር እና በህዝብ ላይ የሽብር ተግባራትን በመፈፀም ላይ በመሆናቸው በሽብርተኝነት መፈረጃቸው አግባብ መሆኑን በመጠቅስ ነበር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳቡን እንዲያፀድቀው አቅርቦ ነበር፡፡

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 መሠረት “ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ውሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙም ሲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳቡን ማቅረቡ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.