Fana: At a Speed of Life!

የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ሙዚየም ማቋቋም በትውልዱ ላይ የሃገር ፍቅር ስሜት ለማስረጽ አቅም እንደሚኖረው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ወታደራዊ ሙዚየምን ማቋቋም በትውልዱ ላይ የሃገር ፍቅር ስሜት ለማስረጽ ትልቅ አቅም እንደሚኖረው ተገለጸ።

የወታደራዊ ቅርስ ጥበቃና ወታደራዊ ሙዚየም በኢትዮጵያ በሚኖረው ፋይዳ፣ ተግዳሮትና መልካም አጋጣሚዎች ዙሪያ የምክክር አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።

በአውደ ጥናቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት፣ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ተወካዮችና የቀድሞ ሰራዊት አባላት አባላት ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት ባለፈው ትውልድና በአሁኑ ትውልድ በወታደሩ እየተከፈለ ያለውን መስዋዕትነት ለመዘከር ወታደራዊ ወመዘክር ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።

በተለይም ወታደራዊ ሰነዶችን በአግባቡ መሰነድ እና ሙዚየም ማደራጀት በህብረተሰቡ እና በሰራዊቱ መካከል መቀራረብ እንዲፈጠር አስተዋጽኦው የጎላ ይሆናል ተብሏል።

በተጨማሪም ለሃገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ አንድ አማራጭ ሆኖ በመምጣት ኢኮኖሚ ፋይዳ ይኖረዋልም ነው የተባለው።

በጥናትና ምርምር ረገድም ግብዓት የመሆን አቅም እንደሚሆን በአውደ ጥናቱ ላይ በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ተመላክቷል።

ለወታደራዊ ቅርስ ማሰባሰቡ እና ወታደራዊ ሙዚየምን በማደራጀቱ ተግባር ሁሉም ሊረባረብ ይገባልም ነው የተባለው።

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.