Fana: At a Speed of Life!

ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በሁለቱ ሃራት የጋራ ጉዳይ ላይ የተወያዩ ሲሆን፥ የሃገራቱን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በዓለም ዓቀፍ ሰላም ማስከበር ላይ የበለጠ መስራት በሚቻልበት አግባብ መክረዋል፡፡
የመከላከያ ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ እንዳሉት ÷ ሁለቱ ሀገራት የቆየ የጋራ ትብብር ስላላቸው በተለይም በሰላም ማስከበር ግዳጅ እና በቴክኖሎጂ ዙሪያ በጋራ ይሰራሉ፡፡
በኢትዮጵያ በህግ ማስከበር ዘመቻ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.