Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን ከ18  ሚሊየን በላይ  የቡና ችግኝ ለተከላ  ተዘጋጀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጌዴኦ ዞን በተያዘው ዓመት ለተከላ የሚበቃ ከ18 ሚሊየን በላይ የቡና ችግኝ መዘጋጀቱን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ገለጹ።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከመምሪያው ጋር በመተባባር ለአካባቢው የቡና ልማት ድጋፍ እያደረገ መሆኑም ተመልክቷል።

በመምሪያው የቡና ልማት ባለሙያ አቶ ምርታገኝው በቀለ ÷ችግኙ የተዘጋጀው በዞኑ የቡና ልማትን ለማስፋፋት በታቀደው መሰረት የሚከናወን ነው ብለዋል።

ከዚህ በፊት ይተከል የነበረው  የቡና ችግኝ ምርት ለመስጠት ሶስት ዓመት  እንደሚፈጅበትና አሁን ለተከላ የተዘጋጀው ዝርያ  ተገቢው እንክብካቤ ከተደረገለት በአንድ ዓመት ውስጥ ምርት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ችግኙ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በመንግስት የችግኝ ጣቢያዎችና በአርሶ  አደር ማሳ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።

ያረጁ ቡናዎች ነቀላ ፣የጉድጓድ ቁፋሮና የአፈር ማልበስ ስራ እንዲሁም የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ላጠናቀቁ አርሶ አደሮች ከተዘጋጀው ችግኝ በማሰራጨት እየተተከለ  እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ በበኩላቸው÷ ተቋሙ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ጋር በትብብር እየሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.