Fana: At a Speed of Life!

“ቱሪዝም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ” በሚል መሪ ቃል የጥናትና ምርምር  ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆቴልና ቱሪዝም  ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር  “ቱሪዝም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል  የጥናትና ምርምር  ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ፕሮግራም መክፈቻ ላይ   ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት  ሚኒስትር ዴኤታ እና የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ቦርድ ሰብሳቢ÷  የቱሪዝም ዘርፉ ለዘላቂ ልማት ግብ ያለውን የጎላ ድርሻ አንስተዋል።

ፕሮፌሰር አፈወርቅ አክለውም  ቱሪዝም ከኢኮኖሚ ዘርፍ አንዱ በመሆኑ ከሆቴል ማህበራት፣ ከትምህርት ተቋማት፣ከማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችና ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የቱሪዝም ትስስር ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ምርምር  በማድረግ ዘርፉን ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል ።

ዶክተር ሂሩት ካሳው  የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የቱሪዝም መስህብ የማይሆን ምንም ነገር የለም ።

ከኛ የሚጠበቀው የዘርፉ  ሙሁራንን በመጠቀም  በጥናት የተደገፈ  ሥራ በስፋት ማስተዋወቅ እና ማልማት ነው ማለታቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት  ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.