Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ሁሉ ድጋፏ ያልተለየ ወዳጅ ሃገር ናት -ዶክተር ባርናባ ማሪያ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ሁሉ ድጋፏ ያልተለየ ወዳጅ ሃገር መሆኗን የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ባርናባ ማሪያ ቤንጃሚን ገለጹ።

ሚኒስትሩ በደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ጋር በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በወቅቱም አምባሳደር ነቢል ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ አብራርተዋል።

አያይዘውም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ሂደትና የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲሁም ስለመጪው ብሔራዊ ምርጫ አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።

ዶክተር ባርናባ ማሪያ ቤንጃሚን በበኩላቸው የሃገራቱን ግንኙነት ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ሁሉ ድጋፏ ያልተለየ ወዳጅ ሃገር መሆኗን አውስተዋል።

አክለውም ሃገራቱ በቀጠናው በጋራ መልማት እንዲችል በመንገድ፣ በኤክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማት እና ሌሎችም ወሳኝ መሰረተ ልማቶች መተሳሰር የሚያስችሉ ትብብሮች መጠናከር አለባቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ያላትን ያልቋረጠ ድጋፍ አድንቀው፥ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ገቢራዊ እንዲሆን በኢትዮጵያ በኩል ቀጣይ ድጋፍ እንዲደረግ ዶክተር ባርናባ ማሪያ ቤንጃሚን መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.