Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ለአርሶ አደሮችና ለኢንተርፕራይዞች የ950 ትራክተሮችን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል በአራተኛው ዙር 950 ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች የማስረከቢያ መርሃ ግብር በሻሸመኔ አካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ አባ ገዳዎችን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ክልሉ ግብርናን ለማዘመን ከሚሰራው የቆላ ስንዴ፣ የአቮካዶ፣ የማር ማምረት ስራዎች በተጨማሪ የማረሻ ትራክተሮችንም ለአርሶ አደሩ በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል።
ትራክተሮቹ ኬኛ በተሰኘው ፋብሪካ በሃገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ሲሆን ፋብሪካዉ ከሁለት ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ግብአቶችን በማስመጣት በሃገር ውስጥ ይገጣጥማል፡፡
የክልሉ መንግሥት በሶስት ዙሮች 737 ትራክተሮችን ለአርሶ አደሩ ያደረሰ ሲሆን በአራተኛው ዙር 950 ትራክተሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ 687 ትራክተሮችን ማከፋፈሉ ታውቋል፡
ቀሪ የተዘጋጁ 450 ትራክተሮች ደግሞ በቀጣይ ቀናት ለአርሶ አደሩ ይከፋፈላሉ ነው የተባለው።
ክልሉ የማረሻ ትራክተሮችን ከመስጠት በተጨማሪ በቀጣይ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ሊደረግ የታቀደውን ለአርሶ አደሩ አመቺ ያልነበሩ የባንክ ብድር አወሳሰድን ማስተካከል እና አርሶ አደሩ የማረሻ ትራክተሩን አስይዞ ብድር እንዲያገኝ የማድረጉ ተግባር በኦሮሚያ ደረጃ ማስጀመሩም ታውቋል።
በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር ሴክተር ሃላፊ ዶክተር ግርማ አመንቴ እንዳሉት፥ በክልሉ ግብርናን ለማዘመን እና ፋይናንስን በሰፊው ወደ ገጠር ለማስገባት እየተሰራ ነው፡፡
በኦሮሚያ ክልል 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ቢኖርም እስካሁን በሜካናይዜሽን የታረሰው 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር ወይም 20 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው።
በፍሬህይወት ሰፊውና በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
116,620
People Reached
9,005
Engagements
Boost Post
1.6K
347 Comments
119 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.