Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በየካ ክፍለ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ 117 ዜጎች መኖሪያ ቤቶችን አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በየካ ክፍለ ከተማ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 117 ዜጎች የቀበሌ መኖሪያ ቤቶችን አስተላለፉ።
ለወጣቶችና ሴቶች ሥራ ዕድል ለመፍጠርም 26 የንግድ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል።
በክፍለ ከተማው ለ117 ዜጎች የተላለፉት መኖሪያ ቤቶች 468 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው።
የንግድ ቤቶቹ ደግሞ 130 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆናቸው ተገልጿል።
በቀጣይ ሳምንት የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓል በማስመልክትም ለ120 የእስልምና እምነት ተከታዮች የበግ እና ሌሎች የምግብ ቁሳቁሶች ምክትል ከንቲባዋ ማበርከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የከተማ አስተዳደሩ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የቀበሌ ቤቶችን በማስመለስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ እና ለአካል ጉዳተኞች ማስተላለፉ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
49,425
People Reached
1,714
Engagements
Boost Post
683
26 Comments
20 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.