Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ምርት ገበያና የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያና የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የሃገሪቱን የማዕድን ምርቶች ለማገበያየት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት በጋራ ለመቀየስ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግና የሃገሪቱን የወጪ ንግድ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህን ጥረት አጠናክሮ ለመቀጠልም ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ጋር የሃገሪቱን የማዕድን ምርቶች ለማገበያየት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት በጋራ ለመቀየስ የመግባባቢያ ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል፡፡

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ገበያን የሚያሳድግ፣ ህገወጥ ንግድን መቆጣጠርና መቀነስ የሚያስችል እንዲሁም ወጥ የሆነና ዘላቂ የገበያ ስርአትን መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.