Fana: At a Speed of Life!

በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን የክልል መንግስታት ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልል መንግስታት ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል ለሰላም መኖር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልሎች የጎንዮሽ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጠናከርና የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ከደቡብ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
ሰላም እንዲሰፍን በክልሎች መካከል የመንግስታት ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የምክር ቤቱ የዴሞክራሲ አንድነት፣ የሕገ መንግስት አስተምህሮና የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፀሃፊ አቶ ሽብሩ እሸቱ ተናግረዋል፡፡
የመንግስታት ግንኙነት በአካባቢው የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በውይይት፣ በድርድርና መተማመንን በሚያጎለብት መልኩ ለመፍታት እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ምርጥ አካባቢያዊ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ የጋራ ፕሮጀክቶችን በመተግበር የአካባቢውን ማህበረሰብ የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስችላልም ነው ያሉት፡፡
የመንግስታት ግንኙነት የሚመራበት የታወቀና ውጤታማ የአሰራር ስርዓት አለመዳበር እንደ ችግር ሲነሳ የቆየ ቢሆንም፥ አሁን ላይ የመንግሥታት ግንኙነት የሚመራበት ራሱን የቻለ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ መውጣቱን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ አዋጅ በተቀመጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት እቅዶችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አብራርተዋል፡፡
ተሳታፊዎች በክልላቸውና በአጎራባች ክልሎች የሚታዩ ችግሮችን በጥናት መለየት፣ የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ተቋም መመስረትና የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን መስራት እንደሚኖርባቸውም አንስተዋል፡፡
በስልጠናው የደቡብ ፣ ሲዳማ፣ የአፋር፣ የኦሮሚያ፣ የሶማሌ እና የጋምቤላ ክልሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች መካፈላቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
15,889
People Reached
484
Engagements
Boost Post
277
10 Comments
12 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.