Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቶች ከ119 ሺህ በላይ ለሆኑ መዛግብት እልባት ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፍርድ ቤቶች በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለ119 ሺህ 413 መዛግብት እልባት መስጠታቸውን የሶስቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አመለከተ፡፡
በሪፖርቱ በሶስቱም ፍርድ ቤቶች በበጀት ዓመቱ ዕልባት እንዲያገኙ ከተያዙ መዛግብት በዘጠኝ ወሩ 118 ሺህ 417 መዛግብት ዕልባት እንዲያገኙ ታቅዶ 119 ሺህ 413 መዛግብት ዕልባት ማግኘታቸው ታውቋል፡፡
አፈጻጸማቸውም 100 ነጥብ 8 በመቶ መድረሱን ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ይህ አፈጻጸም በዘጠኝ ወሩ ለየፍርድ ቤቶች ተይዘው ከነበሩ ዕቅዶች አንጻር ሲታይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለ11 ሺህ 648 መዛግብት እልባት ለመስጠት ታቅዶ 10 ሺህ 238 መዛግብት ዕልባት በማግኘታቸው አፈጻጸሙ 87 ነጥብ 89 በመቶ ሲሆን፥ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ19 ሺህ 777 መዛግብት እልባት ለመስጠት ታቅዶ 19 ሺህ 172 መዛግብት ዕልባት በማግኘታቸው አፈጻጸሙ 96 ነጥብ 94 ደርሷል ነው የተባለው፡፡
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ደግሞ ለ86 ሺህ 992 መዛግብት እልባት ለመስጠት ዕቅድ ተይዞ ለ90 ሺህ 3 መዛግብት ዕልባት በመሰጠቱ አፈጻጸሙ 103 ነጥብ 4 በመቶ የደረሰ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.