Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል ከ2 ነጥብ 1ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀረሪ ክልል በዘንድሮ የክረምት ወራት የአረንጋዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከ2 ነጥብ 1ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡
የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድርና የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአረንጋዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከማሳካት አንጻር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በዘንድሮ በጀት አመት 60 በመቶ የሚሆኑ የፍራፍሬ ችግኞችና 40 በመቶ የሚሆኑ ደግሞ የዛፍ ችግኞች እንደሚተከሉ የገለጹት ምክትል ርእሰ መስተዳድሯ በክልሉ የአረንጋዴ አሻራ ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት 2 ነጥብ 1ሚሊየን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
ችግኞችን ከማልማት ጋር በተያያዘ የችግኞችን የመጽደቅ መጠንን ከማሻሻልና ከማሳደግ አንጻር በትኩረት እንደሚሰራም ነው የተናገሩት፡፡
የአረንጋዴ አሻራ ልማትን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ በመግለጽ ለችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ200 ሺህ በላይ የችግኝ ጉድጓዶች ተቆፍረው ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
በክልሉ በ2012 በጀት አመት 2 ነጥብ 5ሚለየን ችግኞችን ለመትከል ታስቦ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች መትከል መቻሉን ከዚህም ውስጥም 87 በመቶ መፅደቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.