Fana: At a Speed of Life!

የሸኔን እንቅስቃሴ ለማምከን የፌደራል ፖሊስ አባላት ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር እየሰሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ዞን የአሸባሪዉ ሸኔን እንቅስቃሴ ለማምከን የፌደራል ፖሊስ አባላት ከአካባቢው ሚሊሻና ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት እየሰሩ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በዞኑ የሚንቀሳቀሰዉን የሸኔ ቡድን በአካባቢዉ ያሉ ነዋሪዎችን በመግደል፣ በማፈናቀል፣ ንብረት በማዉደምና በመዝረፍ አካባቢዉን የሽብር ቀጠና ለማድረግ የሚሰራዉን ስራ ለመግታትና ለማስቆመ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ስምሪት በመስጠት የፖሊስ አባላቱ ወደ በወለጋ ሆሮ ገድሩ ዞን በመግባት የአሸባሪዉን ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለማስቆም የላቀ ሚና እየተወጡ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
ሰሞኑን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የተመራ ልዑክ ወደ አካባቢዉ በመሄድ በቦታዉ ግዳጅ ላይ ካሉ አባላት እንዲሁም ከአካባቢዉ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል፡፡
በዉይይቱም የዞኑን ሰላም ለማስፈን የሸኔን ህግ ወጥ እንቅስቃሴ ለማስቆም የአካባቢዉ አስተዳደር ዉስጥ ያሉ ችግሮችን በአግባቡ መፈተሽና መለየት እንደሚገባ ተነስቷል፡፡
በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ዞን ግዳጅ ላይ የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ከአካባቢዉ አስተዳደርና የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩ ያላቸዉን ቁርጠኝነት መግለፃቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.