Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የሞጆ-መቂ-ባቱ የመንገድ ፕሮጀክትን መረቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሞጆ -ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የሞጆ- መቂ- ባቱ የመንገድ ፕሮጀክትን መረቁ፡፡

ፕሮጀክቱ 92 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከሞጆ-መቂ 56 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ፣ ከመቂ ባቱ ያለው ደግሞ 37 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል።
ከዚህ ባለፈም መንገዱ 32 ሜትር ስፋት አለው።

ለመንገድ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ቀንድ ትስስር አካል ሲሆን ኢትዮጵያ ከቀጠናው ሃገራት ጋር ላላት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል በጅቡቲ ወደብ ላይ ተንጠልጥሎ የቆየውን የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ምርቶች እንቅስቃሴ አማራጭ በማስፋትም ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን በስፋት እንድትጠቀም የመንገዱ ግንባታ ድርሻው የጎላ ይሆናል ተብሏል።

መንገዱ የአዲስ አበባ – ሞያሌ – ናይሮቢ – ሞምባሳ እንዲሁም 10 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውና ከግብጽ ካይሮ ተነስቶ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ድረስ የሚዘልቀው የትራንስ አፍሪካ ሃይዌይ የመንገድ ትስስር አካልም ነው።

የመንገዱ ግንባታ ቀጣይ ክፍል የሆነው የባቱ-አርሲ-ነገሌ-ሐዋሳ የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል።

መንገዱ በአካባቢው የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን ለገበያ በፍጥነት ለማቅረብ እንዲሁም በመስመሩ የሚገኙ ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችም ተጠቃሚ ይሆኑበታል ነው የተባለው።

ከቱሪዝም አኳያም በመስመሩ የአቢያታ፣ሻላ፣ የላንጋኖና የሐዋሳ ሃይቆች በመኖራቸው ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሃገር ጎብኚዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.