Fana: At a Speed of Life!

ለሁሉም ዜጋ እኩል የምትመች ሀገር እየገነባን ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 9 ቢሊየን ብር በሚጣጋ ወጪ የተገነባው የቡልቡላ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፖርክ ተመርቋል፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፣ የህዝብ ተካወዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች እና የአካባቢ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ለሁሉም ዜጋ እኩል የምትመች ሀገር እየገነባን ነው ያሉ ሲሆን እኛ በርትተን እንሰራለን፣ ጠላቶቻችን ነገ ተንበርክከው  ይቅርታ ይጠይቃሉ ብለዋል።

እርሻ ካልዘመነ እና ካልተቀየር  የአርሶ አደሩ ህይዎት እና  የኢትዮጵያ  አትቀየርም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነው የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ሕይዎት ለመቀየር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ተግቶ በመስራት፣በመውደድ እና ሰላምን በማስጠበቅ  ሁሉን ማቀፍ የምትችል ኢትዮጵያን እንገነባለን ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው በተለያየ ምክንያቶች ተጓቶ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ በከፍተኛ ክትትል እና ድጋፍ ለምርቃት መብቃቱን በመግለፅ ለአከባቢው ማህበረሰብ እና ለሀገር ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡

የአርሶ አደሩን ህይወት መለወጥ እና ገጠርን ማልማት ከድህነት መውጫ መንገድ በመሆኑ በትኩረት መሰራት ያሰፈልጋል ሲሉ አቶ ሽመልስ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፤  አርሶ አደሮችን የግብር ምርታቸውን በቀላሉ ለኢንዱስሪ ፓርኩ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ነው ያሉት።

የአካባቢው ወጣቶችም የስራ እድል ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።

ፓርኩ ለሞጆ ደረቅ ወደብ፣ለአዲስ አበባ እና ለፈጣን መንገድ ቅርብ በመሆኑ የአርሶ አደሮቻችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ  ብለዋል።

ግብዓት አቅርቦት እና አስተማማኝ ሰላም መኖር አስፈላጊ መሆኑን አክለዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.