Fana: At a Speed of Life!

ጎንደር እና አዲስ አበባ የእህትማማች ከተማ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር እና አዲስ አበባ ከተሞች የእህትማማች ከተማ ግንኙነት ምስረታ ስምምነት ተፈራረሙ።

የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ማስተዋል ስዩም እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባኢንጂነር ታከለ ኡማ ናቸው ስምምነቱን የተፈረመውት።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሰው እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የኤርትራ ልዑካን በእህትማማችነት ግንኙነት ምስረታ ፊርማ ስነ ስርአቱ ተገኝተዋል።

ስምምነቱ ከተሞቹ በመንገድ፣ በሰው ሃብት ልማትና ዓቅም ግንባታ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ ልማትና አቅርቦት፣ በቱሪዝም መስፋፋት፣ በባህል ልማት በከተማ ገፅታ ግንባታ ዘርፎች ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ ጥቅም ላይ ማዋላ ላይ ያተኩራል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለኢንጂነር ታከለ ኡማ የጃኖና ካባ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ በቀጣይም መሰል የእህትማማችነት ግንኙነት ምስረታውን ከሌሎች የሃገሪቱ ከተሞች ጋርም ለመፈራረም ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል።

በሶዶ ለማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.