Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሆስፒታልና ሁለገብ ህንጻ የግንባታ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ሆስፒታል እና ሁለገብ ህንጻ ግንባታ ስራን አስጀምረዋል፡፡
ምክትል ከንቲባዋ የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ይሄን ሁለገብ ህንፃ ለመገንባት ማቀዱ ሊመሰገን እና ሊበረታታ ይገባል ያሉ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።
ይህ የሆስፒታል እና ሁለገብ ህንጻ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ባለዘጠኝ እና ባለ ስድስት መንትያ ህንጻዎች እንደሚኖሩት ታውቋል፡፡
በሆስፒታሉ በስፔሻላይድ ደረጃ ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል የጤና ተቋምም በውስጡ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ማህበር ለሆስፒታል እና ሁለገብ ህንጻ መገንቢያ 3 ሺህ 600 ካሬ ሜትር መሬት ከሊዝ ነጻ የሰጠ ሲሆን ይህም የመምህራንን መብትና ጥቅም ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።
የህንጻው ግንባታ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የሚገነባ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.