Fana: At a Speed of Life!

8ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)8ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሁነቶች ተከበረ፡፡
በመርሃ ግብሩ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት የትራፊክ አደጋ ችግርን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የእግር ጉዞና እና የብስክሌት ትራንስፖርትን ለማበረታታት “ከጳጕሜን እስከ ጳጉሜን #እንደርሳለን!” በሚል የተጀመረውን ንቅናቄ ለማስቀጠል ለ8ተኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ማለትም የእግር ጉዞ፣ የሳይክል ትራንስፖርት እና በካይ ያልሆኑ የህዝብ ትራንስፖርቶች የማስተዋወቅና ለህብረተሰቡ ለማመቻቸት የተጀመሩ ስራዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።
የሞተር አልባ ትራንሰፖርት አማራጮችን ለአጫጭር ጉዞዎች መጠቀም የትራፊክ አደጋን ከመከላከል፣ የአምሮን ጤንነትን ከማሻሻል ፣ የአየር ብክለትን ከመቀነስ አንጻር እንዲሁም የፓርኪንግ ችግርን ከማቃለል አንጻር ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳለው ወይዘሮ ዳግማዊት መናራቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.