Fana: At a Speed of Life!

ፌዴራል ፖሊስ በ19ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 431 የፖሊስ አባላት አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በ19ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 431 የፖሊስ አባላት አስመርቋል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መስፍን አበበ ተገኝተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ኮማንደር ፍቃዱ ጉደታ የመሰረታዊ ፖሊስ ስልጠና ምክትል ዳይሬክተር ተልዕኮውን ለመፈፀምና ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር በአዕምሮው የበሰለ፣በአካል የጠነከረና በስነ-ምግባር የታነፀ፣ለህዝብና ለህገ-መንግስቱ የቆመና የህገ-መንግስታዊ መሰረታዊ መብቶችንና ነፃነቶችን የሚያከብርና የሚያስከብር የፖሊስ ሀይል ወቅቱ የሚያስፈልገው ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወገንተኝነት የፀዳ፣ የዜጎችን ህይወትና ንብረት ለመጠበቅ ሲል እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ቁርጠኛ የሆነ የፖሊስ ሀይል አሰልጥኖ ለተልዕኮው ብቁ አድርጎ ወደ ስራ ማሰማራት ወሳኝ መሆኑ መግለፃቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምልምል የፖሊስ አባላቱ ቀጣይ በሚሰማሩበት ፖሊሳዊ ሙያ ብቁ ሆነው የተሰጣቸውን ሙያዊ ሃላፊነት በሚገባ ለመወጣት እንዲችሉ በቆይታቸው ስልጠና የተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.