Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሁሉም ትብብርና ጥረት ያስፈልጋል – ሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው ከመተከል ዞኑ ኮማንድ ፖስትና አመራሮች እንዲሁም ከአማራ ክልል አዊ ዞን አመራሮች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።
ወይዘሮ ፍሬዓለም በውይይቱ እንዳሉት፤ አካባቢውን ወደ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት በምክክርና በቅንጅት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የሚመሰገኑ ናቸው።
በመሆኑም በመተከል ዞን የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ የአመራሩ፣ የፀጥታ ሃይሉና የማህበረሰቡ ትብብር መቀጠል አለበት ብለዋል።
የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በመንግስት በኩል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ ከባለሀብቶች፣ ከተለያዩ ድርጅቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረሃይል ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመመለስ ሂደት የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ለየወረዳዎች መላኩን ገልፀው ወረዳዎች የሚሰሩትን በመገምገም ዜጎችን የመመለስ ስራው እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዳይመለሱ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰው፤ “ዜጎችን መመለሱ የስነልቦና ሥራ ጭምር የሚጠይቅ በመሆኑ በቅንጅት መስራት ይገባል” ብለዋል።
የአዊ ዞን ጓንጓ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ዓለሙ በበኩላቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን የመመለሱ ጥረት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊ ሎጂስቲክስና መሰል አቅርቦቶች ሊታሰብባቸው እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.