Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን የገጠሟትን ፈተናዎች በድል ለመሻገር በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሊቆሙ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን የገጠሟትን ፈተናዎች በድል ለመሻገር በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሊቆሙ እንደሚገባ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ  ላይ ያተኮረ በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት በተቋቋሙ ሶስት ማህበራት  አስተባባሪነት ውይይት ተካሂዷል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በውይይቱ ላይ እንዳሉት÷ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ላደረገችላቸው ጥሪ ሁሉ ፈጣንና ቀና ምላሽ እየሰጡ ነው።

ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ ከሱዳን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ፣ የሃሰት መረጃ ስርጭት፣ የዜጎች መፈናቀልና ጥቃት እንዲሁም ከቀጣዩ ብሔራዊ ምርጫ  ጋር በተገናኘ የሚደረጉ  ጫናዎችን በመመከት ረገድ የዳያስፖራው ሚና ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የማህበራት አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎችም÷ ከአገር ውስጥም ከውጭም የአገርን አንድነትና ሰላም ለማናጋት እየሰሩ ያሉ ኃይሎችን ከምንጊዜውም በላይ እንደሚታገሏቸው ቃል ገብተዋል።

የውይይት መድረኩን ያስተባበሩት ኢትዮጵያ ትቀጥላለች፣ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ዲያስፖራ ማህበረሰብ እና ኦሞ ኢትዮጵያ አንድነትና ፍትህ ማእከል መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.