Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ተመረቁ።

የተመረቁት ሆስፒታሎች ደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ የሚገኘው ኮይቬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና በደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኘው ጋዘን የመጀመሪ ደረጃ ሆስፒታል መሆኑ ተመላክቷል ::

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል ለማድረስ እና የሆስፒታሎችን አቅም በማሳደግ የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት  ለማስፋት በሃገር ደረጃ ሰፊ ስራ እየተሰራ ብለዋል፡፡

በክልሉ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ በጂንካ ደረጃውን የጠበቀ ላብራቶሪ እንደሚገነባ ገልፀው÷ በድንበር አካባቢዎችም የጤና አገልግሎቱን ለማድረስ እየተሰራ  መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ማህበረሰቡን ከወረርሽኝ በሽታዎች ለመከላከል የወረርሽኝ መከላከያና መቆጣጠርያ ማዕከላት ይገነባሉም ነው ያሉት፡፡

በሆስፒታሎቹ እየተሰጠ ያለውን የጤና አገልግሎት ሚኒስትሯ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን÷ በተለይም በድንገተኛና ፅኑ ህክምና፣ በቀዶ ህክምና እና በእናቶችና ህፃናት ጤና ዙሪያ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት የሚበረታታ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በሆስፒታሎቹ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችንና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞችንም  ማመስገናቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.