Fana: At a Speed of Life!

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

ከተማ አስተዳደሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።  የመግለጫው ሙሉቃል እንደ ሚከተለው ቀርቧል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸዉና ከምትከበርባቸዉ ሀገራዊ ልዩ እሴቶቿ ዉስጥ አንዱ የዘርፈ ብዙ ልዩነቶች የመቻቻል ምድር መሆኗ ሲሆን ህዝቦቿ በፈሪሃ አምላክ የሚመሩ ናቸዉ፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን የሀይማኖት ብዝሃነትን በመቻቻል፣ በአብሮነትና በመከባበር የሚያስተናግድ ማህበረሰብ ያላት ታሪካዊ ተምሳሌት መሆኗ ነዉ፡፡

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች፣

የእስልምና ኃይማኖትና ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ከከተማችሁ አዲስ አበባ ጋር ያላቸዉ ታሪካዊ ትስስር በማይናወጥ መሠረት ላይ የተጣለዉ ገና ከጅምሩ በመሆኑ ከእምነት ጋር ተያይዞ ለዘመናት ሲያጋጥሙን ለኖሩት የዉስጥና የዉጪ ተግዳሮቶች ሳንበገር አንድነታችንን፣ አብሮነታችንን፣ ሉዓላዊነታችንንና ተቻችሎ በፍቅር የመኖር እሴቶቻችንን በጥበብና በጀግንነት አስጠብቀን ኖረናል፡፡

የዚህ ማንነታችን ቀጣይ የሆነዉን ዛሬያችንን በፍቅርና በክብር አብረን በማሳለፍ ላይ እንገኛለን፡፡

ዘንድሮ የታላቁን የረመዳን ጾም ወቅት በታሪካችን ከእናትና ከአባቶቻችን የወረስነዉን እሴት በማስጠበቅ በተለያየ መልኩ በየቦታዉ አብረን አሳልፈናል፡፡

ለአብነትም በቅርቡ የሰጠነው የማምለኪያ ቦታዎች ይህንን ይመሰክራሉ።በስካይ ላይት ሆቴል ሁሉም ሃይማኖቶች በተገኙበት ከሙስሊም ወንድሞቻችን ጋር አብረን አፍጥረናል፡፡ ከሶሪያዊያን ተፈናቃይ ወንድምና አህቶቻችን ጋር እንዲሁ፡፡ በቤተ-መንግስት፣ በሆቴሎችና በየክፍለ ከተሞቻችን ማዕዶችን ተጋርተናል፡፡ በፍቅርና በመከባበርም አብረን አሳልፈናል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የዘንድሮዉን የረመዳን ጾም ልዩ በሚያደርግ ሁኔታ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ሰፋፊ የጎዳና ላይ የአፍጥር ፕሮግራሞች እጅግ በሚያስደስትና ጠላቶቻችንን በሚያስቀና ሁኔታ በመንግስት አካላት እና በሁሉም ነዋሪዎች ትብብርና አብሮነት ሲካሄዱ ቆይቷል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ቁጥር ያለዉ የሙስሊሙን ማህበረሰብና ሌሎችን ያሳተፈ የጎዳና ላይ አፍጥር ለማካሄድ የተዘጋጀዉ እቅድ ባዘጋጁ አካላትና ግለሰቦች እንድናዉቀዉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ፕሮግራሙ በተሳካና የዓለም ሪከርድ በሚሰብር ሁኔታ እንዲፈጸም ከፍተኛ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፡፡

ከአዘጋጆቹ ጋር በተደጋጋሚ እየተገናኘን ለፕሮግራሙ ዉጤታማነት በሙሉ ልባችን ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ለስኬቱም እስከ መጨረሻዋ ድረስ በሙሉ አቅማችን ሰርተናል፡፡

ይህን ትልቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለአብሮነትና ለሀገር አንድነት ለማዋል የተሰራዉ ሥራ የሀሳቡን አመንጪዎችና አዘጋጆቹን የሚያስመሰግን ታላቅ ተግባር መሆኑን እናምናለን፡፡

በእርግጥም ዛሬም በከተማዋ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ የአፍጥር ፕሮግራሞች ተካሂደዋል ።

የተከበራችሁ የከተማችን የእስልምና እምነት ተከታዮች፣አብሮ አንድ ማዕድ በጋራ የተቋደሰ አደባባይ የኔ ያንቴ ብሎ አይጣላም፡፡

ነገር ግን የአደባባዩ የመጨረሻ የግንባታ ሥራዎች አለመጠናቀቃቸዉ፣ ከሥነ-ሥርዓቱ መከናወን ጋር ተያይዞ ተገቢ ያልሆነ የደብዳቤ ልዉዉጦች ካደረጉት አካላት ጋር በመወያየት በጋራ ግንዛቤና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተና ያለንበትን አጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ ፕሮግራሙ በታቀደዉ መሠረት የኢፍጣር ቦታዉ ስፋቱና ርዝመቱ እንዲያሳትፈዉ ከታሰበዉ የታዳሚ ብዘት አንጻር እንቅፋት እንዳይፈጠር እዛዉ በዉስን አካባቢ እንዲካሔድ እንደመፍትሔ ተወስዶ ነበር፡፡

እንደፍላጎታችን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በመድረኩ ላይ ተገናኝተን በባህላችናና በታሪካችን መሠረት ፕሮግራሙን በአብሮነትና በፍቅር ባከበርን ነበር፡

ሆኖም አዘጋጆቹ የኢፍጣር ቦታዉ ስፋቱና ርዝመቱ ውስንነት ላይ ስላልተሰሙ የመሰረዝ አማራጭን ወስደዋል፡፡

በሌላ በኩል ይህን ለሌላ አላማቸው ለማዋል በማህበራዊ ሚዲያ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዲራገብ ያደረጉ አካላት እንዳሉ አስተውለናል።ይህም የተወሰነ ቅሬታን መፍጠሩን እንገነዘባለን፡፡

ዉድ ሙስሊም ወገኖቻችን በተለያዩ ድምር ምክንያቶች በተፈጠረዉ የፕሮግራሙ መስተጓጎል ቅሬታ ሊፈጥር የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅሬታችንን የምንገልጽበት መንገድም በሰላማዊና በሰከነ አግባብ መሆን ይኖርታል፡፡

ከሌሎች እምነት ተከታይ ወንደሞቻችን ጋር ሆነን ለዘመናት ነብሳችንን ገብረን ያቆየናትን ሀገራችንን ለጥቃት ማገላጥ አይገባንም፡፡

ስለሆነም ሌሎች ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ለሺ ዓመታት የምናከብርባትን ታላቋን ዲሞክራሲያዊትና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት እየተደረገ ያለዉን ርብርብ ለማደናቀፍ እየሰሩ ላሉ አካላት ዕድል እንዳንሰጥ እንደ እምነቱ አስተምህሮት ታጋሽነታችሁን ታጸኑ ዘንድ አደራ እንላለን፡፡

የተፈጠረዉን ከፍተት በመጠቀም የግል ጥቅማችሁንና ፍላጎታችሁን ለማሳካት ሲባል ጨዋዉን ህብረተሰብ ለማሳሳትና በማይገባ ተግባር ላይ ለማሳተፍ የምትጥሩ ግልሰቦችና አካላትም ከድርጊታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ እናሳስባለን፡፡

ወቅቱ በእልህና ለጠላቶቻችን ክፍተት በሚፈጥር መልኩ መሆን የለበትም በማለት ይሄንኑ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ ህዝበ ሙስሊሞች በሙሉ የከተማ አስተዳደሩ ምስጋናውን ያቀርባል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸዉና ከምትከበርባቸዉ ሀገራዊ ልዩ እሴቶቿ ዉስጥ አንዱ የዘርፈ ብዙ ልዩነቶች የመቻቻል ምድር መሆኗ ሲሆን ህዝቦቿ በፈረሃ አምላክ የሚመሩ ናቸዉ፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን የሀይማኖት ብዝሃነትን በመቻቻል፣ በአብሮነትና በመከባበር የሚያስተናግድ ማህበረሰብ ያላት ታሪካዊ ተምሳሌት መሆኗ ነዉ፡፡

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች፣
የእስልምና ኃይማኖትና ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ከከተማችሁ አዲስ አበባ ጋር ያላቸዉ ታሪካዊ ትስስር በማይናወጥ መሠረት ላይ የተጣለዉ ገና ከጅምሩ በመሆኑ ከእምነት ጋር ተያይዞ ለዘመናት ሲያጋጥሙን ለኖሩት የዉስጥና የዉጪ ተግዳሮቶች ሳንበገር አንድነታችንን፣ አብሮነታችንን፣ ሉዓላዊነታችንንና ተቻችሎ በፍቅር የመኖር እሴቶቻችንን በጥበብና በጀግንነት አስጠብቀን ኖረናል፡፡

የዚህ ማንነታችን ቀጣይ የሆነዉን ዛሬያችንን በፍቅርና በክብር አብረን በማሳለፍ ላይ እንገኛለን፡፡

ዘንድሮ የታላቁን የረመዳን ጾም ወቅት በታሪካችን ከእናትና ከአባቶቻችን የወረስነዉን እሴት በማስጠበቅ በተለያየ መልኩ በየቦታዉ አብረን አሳልፈናል፡፡

ለአብነትም በቅርቡ የሰጠነው የማምለኪያ ቦታዎች ይህንን ይመሰክራሉ።በስካይ ላይት ሆቴል ሁሉም ሃይማኖቶች በተገኙበት ከሙስሊም ወንድቻችን ጋር አብረን አፍጥረናል፡፡

ከሶሪያዊያን ተፈናቃይ ወንድምና አህቶቻችን ጋር እንዲሁ፡፡ በቤተ-መንግስት፣ በሆቴሎችና በየክፍለ ከተሞቻችን ማዕዶችን ተጋርተናል፡፡ በፍቅርና በመከባበርም አብረን አሳልፈናል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የዘንድሮዉን የረመዳን ጾም ልዩ በሚያደርግ ሁኔታ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ሰፋፊ የጎዳና ላይ የአፍጥር ፕሮግራሞች እጅግ በሚያስደስትና ጠላቶቻችንን በሚያስቀና ሁኔታ በመንግስት አካላት እና በሁሉም ነዋሪዎች ትብብርና አብሮነት ሲካሄዱ ቆይቷል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ቁጥር ያለዉ የሙስሊሙን ማህበረሰብና ሌሎችን ያሳተፈ የጎዳና ላይ አፍጥር ለማካሄድ የተዘጋጀዉ እቅድ ባዘጋጁ አካላትና ግለሰቦች እንዲናዉቀዉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ፕሮግራሙ በተሳካና የዓለም ሪከርድ በሚሰብር ሁኔታ እንዲፈጸም ከፍተኛ ጥረት ሲናደርግ ቆይተናል፡፡

ከአዘጋጆቹ ጋር በተደጋጋሚ እየተገናኘን ለፕሮግራሙ ዉጤታማነት በሙሉ ልባችን ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ለስኬቱም እስከመጨረሻዋ ድረስ በሙሉ አቅማችን ሰርተናል፡፡ ይህን ትልቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለአብሮነትና ለሀገር አንድነት ለማዋል የተሰራዉ ሥራ የሀሳቡን አመንጪዎችና አዘጋጆቹን የሚያስመሰግን ታላቅ ተግባር መሆኑን እናምናለን፡፡

በእርጥም ዛሬም በከተማዋ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ የአፍጥር ፕሮግራሞች ተካሂደዋል ።

የተከበራችሁ የከተማችን የእስልምና እምነት ተከታዮች፣አብሮ አንድ ማዕድ በጋራ የተቋደሰ አደባባይ የኔ ያንተ ብሎ አይጣላም፡፡

ነገር ግን በአንድ በኩል የአደባባዩ የመጨረሻ የግንባታ ሥራዎች አለመጠናቀቃቸዉ፣ ከሥነ-ሥርዓቱ መከናወን ጋር ተያይዞ ተገቢ ያልሆነ የደብዳቤ ልዉዉጦች ካደረጉት አካላት ጋር በመወያየት በጋራ ግንዛቤና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተና ያለንበትን አጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ ፕሮግራሙ በታቀደዉ መሠረት የእፍጣር ቦታዉ ስፋቱና ርዝመቱ እንዲያሳትፈዉ ከታሰበዉ የታዳሚ ብዘት አንጻር እንቅፋት እንዳይፈጠር እዛዉ በዉስን አካባቢ እንዲካሔድ እንደመፍትሔ ተወስዶ ነበር፡፡

እንደፍላጎታችን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በመድረኩ ላይ ተገናኝተን በባህላችናና በታሪካችን መሠረት ፕሮግራሙን በአብሮነትና በፍቅር ባከበርን ነበር፡

ሆኖም አዘጋጆቹ የእፍጣር ቦታዉ ስፋቱና ርዝመቱ ውስንነት ላይ ስላልተሰሙ የመሰረዝ አማራጭን ወስደዋል፡፡
በሌላ በኩል ይህን ለሌላ አላማቸው ለማዋል በማህበራዊ ሚዲያ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዲራገብ ያደረጉ አካላት እንዳሉ አስተውለናል።

ይህም የተወሰነ ቅሬታን መፍጠሩን እንገነዘባለን፡፡ ዉድ ሙስሊም ወገኖቻችን በተለያዩ ድምር ምክንያቶች በተፈጠረዉ የፕሮግራሙ መስተጓጎል ቅሬታ ሊፈጥር የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅሬታችንን የምንገልጽበት መንገድም በሰላማዊና በሰከነ አግባብ መሆን ይኖርታል፡፡

ከሌሎች እምነት ተከታይ ወንደሞቻችን ጋር ሆነን ለዘመናት ነብሳችንን ገብረን ያቆየናትን ሀገራችንን ለጥቃት ማገላጥ አይገባንም፡፡

ስለሆነም ሌሎች ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ለሺ ዓመታት የምናከብርባትን ታላቋን ዲሞክራሲያዊትና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት እየተደረገ ያለዉን ርብርብ ለማደናቀፍ እየሰሩ ላሉ አካላት ዕድል እንዳንሰጥ እንደ እምነቱ አስተምህሮት ታጋሽነታችሁን ታጸኑ ዘንድ አደራ እንላለን፡፡

የተፈጠረዉን ከፍተት በመጠቀም የግል ጥቅማችሁንና ፍላጎታችሁን ለማሳካት ሲባል ጨዋዉን ህብረተሰብ ለማሳሳትና በማይገባ ተግባር ላይ ለማሳተፍ የምትጥሩ ግልሰቦችና አካላትም ከድርጊታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ እናሳስባለን፡፡

ወቅቱ በእልህና ለጠላቶቻችን ክፍተት በሚፈጥር መልኩ መሆን የለበትም በማለት ይሄንኑ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ ህዝበ ሙስሊሞች በሙሉ የከተማ አስተዳደሩ ምስጋናውን ያቀርባል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.