Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የደን ሽፋኑን ወደ 17 ነጥብ 2 በመቶ ማሳደግ ተችሏል

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት አመታት የደን መጨፍጨፍን ለመቀነስ በተሰራ ስራ የሀገሪቱን የደን ሽፋን ወደ 17 ነጥብ 2 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ተገለፀ።

ከዚህ ባለፈም በሃገራዊው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አማካኝነት ህዝቡን በማሳተፍ በአራት አመታት ለመትከል ከታቀደው 20 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ እስካሁን 9 ቢሊየን ችግኞች መትከል መቻሉም ተገልጿል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ በመቋቋምና ምላሽ በመስጠት በኩልም፥ ቀላል የማይባል ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የአካባቢ የደንና አየርንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ ተናግረዋል።

በዋናነትም እስከ 2010 ዓ.ም በተገኘው አሃዝ መሰረት ከግብርና ዘርፍ 5 ነጥብ 73 ሜትሪክ ቶን ካርበን፥ ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ዘርፍ 23 ነጥብ 55 ሜትሪክ ቶን ካርበን፣ ከደን ዘርፍ 15 ሜትሪክ ቶን ካርበን፣ ከትራንስፖርት ዘርፍ 0 ነጥብ 34 ሜትሪክ ቶን ካርበን፣ ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ 0 ነጥብ 017 ሜትሪክ ቶን ካርበን እና ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ 0 ነጥብ 03 ሜትሪክ ቶን ካርበን በድምሩ 92 ነጥብ 6 ሜትሪክ ቶን ካርበን መቀነስ መቻሉም ተጠቅሷል።

ከሁለት አመት በፊት በተካሄደ የአፈፃፀም ጥናት መሰረት ከ2002 እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋምና ምላሽ ለመስጠ ከ82 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወይም ከ598 ቢሊየን በላይ ብር ወጪ ተደርጓል ነው የተባለው።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.