Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ፍትሀዊ እንዲሆን የሴቶች ሚና ከፍተኛ ሊሆን ይገባል – ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ሃገራዊው ምርጫ ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ፍትሀዊ እንዲሆን የሴቶች ሚና ከፍተኛ ሊሆን ይገባል አሉ፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሁሉን አቀፍ የሴቶች ንቅናቄ ተካሂዷል፡፡

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ብሎም ህዝቦቿን ከድህነት ለማላቀቅና የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል፡፡

በምርጫው የሴቶች ተሳትፎ መረጋገጥ ይኖርበታልም ነው ያሉት ምንክትል ከንቲባዋ፡፡

ፖርቲው የስራ እድልን ጨምሮ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው በትምህርት ቤት የሕፃናትን ምገባ ተግባራዊ በማድረግም የእናቶችን ድካም እያቃለለ መሆኑንም ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

በንቅናቄው ላይ ከክፍለ ከተማው 13 ወረዳዎች የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ሴት አባላት፣ ደጋፊዎችና የክፍለ ከተማው ሴት ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.