Fana: At a Speed of Life!

በቀን ከ1 ሺህ በላይ ዜጎችን መመገብ የሚችል የምገባ ማዕከል ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ የተገነባውን ሁለተኛ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በይፋ ስራ አስጀምረዋል ።
“አንዳችን ለሌሎች የተስፋ ብርሃን በመሆን መደጋገፍ እና መረዳዳት ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፥ ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ ጊዜ ጀምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን የመደገፍና የመርዳት ተግባራት ሲከናወን መቆየቱን ገልጸዋል

ያለንን ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ካዋልን ብዙ ችግሮቻችን መቅረፍ እንችላለን ያሉ ሲሆን  የምገባ ማእከሉ በቀን አንድ ጊዜ ከ1ሺህ በላይ ዜጎችን መመገብ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንግስት ከለውጡ ወዲህ ዜጎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ስራዎች እየሰራ ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች፥ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተው የምገባ ማእከሉ ዜጎችን መመገብ ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት ስልጠና አግኝተው ራሳቸው እንዲችሉ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩም አቅም የሌላቸው ዜጎች ለመርዳት ፍላጎት ያላቸውን በጎፍቃደኛ ባለሀብቶችን እና ተቋማትን በማስተባበር በአምስት ክፍለ ከተሞች በቋሚነት የምገባ ማዕከል የማደራጀት ስራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.