Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ከፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ከፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ጋር ተወያዩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የፈረንሳይ መንግስት በቅርስ ጥበቃና በከተማ ልማት ዘርፎች ዙሪያ  ለክልሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በአማራ ክልል 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ ለማድረግ የክልሉ መንግስት የሚጠበቅበትን እየተወጣ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ አሁን ላይም ከአጣዬ ምርጫ ጣቢያ ውጭ በክልሉ ያሉ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንና ከ7 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸውንም ገልፀዋል።

በክልሉ ከ500 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ቢኖሩም ከዓለም አቀፉ ማህበረብ የሚደረገው ድጋፍ ጥቂት መሆኑን ለአምባሳደሩ ተናግረዋል።

አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ በበኩላቸው÷ ፈረንሳይና ኢትዮጵያ 125 ዓመታትን ያስቆጠረ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የፈረንሳይ መንግስት በቅርስ ጥበቃና  በሌሎችም የልማት መስኮች ከክልሉ መንግስት ጋር በቅርበት መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በቀጣይም የክልሉን የልማት ፍላጎት መሰረት በማድረግ በአመራር አቅም ማጎልበትና በሌሎች ተግባራት ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንደሚደረጉ መጠቆማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.