Fana: At a Speed of Life!

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርና ፌሌክስ ሲሼኬዲ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የህብረቱ ሊቀመንበር ከአዲስ አበባ ጉብኝታቸው አስቀድሞ በግብጽ ጉብኝት አድርገዋል።
የወቅቱ የህብረቱ ሊቀ መንበር በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል የሚደረገው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት መንገድ ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጥቅምት 18 ቀን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኮንጎ ኪንሻሳ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው አይዘንጋም።
ረጅም አመታትን ያስቆጠረውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናክርም ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ዳግም ለመክፈት ፍላጎት አላት።
በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.