Fana: At a Speed of Life!

በጎርጎራ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች 300 ሄክታር የግንባታ ቦታ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች 300 ሄክታር የግንባታ ቦታ መዘጋጀቱን የጎርጎራ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡

የመሪ ማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ሽጉጥ ለኢዜአ እንደገለጹት÷በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ከቀረቡ 200 ፕሮጀክቶች ውስጥ 136 ተለይተው ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡

የተዘጋጀው የግንባታ ቦታ ላለፉት 20 አመታት በኢንቨስትመንት ስም ታጥሮ የቆየ 175 ሄክታርና ከሶስተኛ ወገን ነጻ የተደረገ 125 ሄክታር ቦታ መሆኑን አመላክተዋል።

በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ጥያቄ ያቀረቡት ባለሀብቶች ከ360 ሚሊየን እስከ 1 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ባለሀብቶቹ ከሚሰማሩባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች መካከል ሎጅዎች፣ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግንባታ እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በስጋና ወተት፣ የማርና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የቀረቡት የኢንቨስትመንት ፕሮጀከቶች እያንዳንዳቸው ከ60 ላላነሱ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥሩ መሆኑን ስራ አስኪያጁ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.