Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የፌዴራል ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የዒድ አል ፈጥር በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በመላ ሀገሪቱ ያለው የክልልና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል ከሌሎች የፌዴራል ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን ነው የገለጸው፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የዒድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ የዒድ አል-ፈጥር በዓል የእምነቱ ተከታዮች እርስ በእርስ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩበት፣ መንፈሳዊ እሴቶቻቸውን የሚያዳብሩበት፣ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር ተቻችለውና ተከባብረው በጋራ መኖርን ለመላው ዓለም የሚያሳዩበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

ይህ ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በርካታ የፀጥታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.