Fana: At a Speed of Life!

ዩኒስኮ የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ  ያግዛል የተባለ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩ መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ የሚያግዝበትን ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል፡፡

የፕሮጀክቱ ስራ መጀመር አስመልክቶ የፕሮጀክቱ ኤክስፐርቶች ፣ በኢትዮጵያ የዩኔስኮ ተወካዮች እና የፕሮጀክቱ ግብረ ሃይል  በበይነ መረብ አማካኝነት  ውይይት ተካሄዷል ፡፡

በኢትዮጵያ የዩኒስኮ ዳይሬክተር ዶክተር  ይሚኮ ዩካዛኪ እንደተናገሩት÷ የፕሮጀክቱ እውን መሆን የኢትዮጵያን ፊልም ኢንዱስትሪ በመጠቀም ያለውን የባህል ብዝሃነት ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተርአቶ ተፈሪ ተክሉ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ፊልም ፖሊሲ እንደ እኤአ በ2017 ይፋ የሆነ እንደሆነ አስታውሰዋል ፡፡

ይህ ፖሊሲ መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ያሳየ እንደሆነም  ገልፀዋል ፡፡

ፖሊሲውን  በዘርፉ ባሉ ህጋዊ ማእቀፍ ሊደግፍና  ተግባራዊነት ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን  አስታውቀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የዘርፉን መዋቅርና ዘርፉን የሚደግፍ ማእቀፍ በማዘጋጀት ሀገሪቱ ፖሊሲውን እንድትተገብር ወደ ሚያስችላት መስመር ያመራል ብለዋል ፡፡

ዩኒስኮ ለዚሁ ተግባር የሚሆን ፈንድ የሚያቀርብ ሲሆን ÷ ለስራው የሚያማክሩ አንድ አለም አቀፋዊና አንድ ሀገራዊ ኢክስፐርት አዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመንግስት ፣ ከሙያ ማህበራት ከግሉ ሴክተር የተወጣጡ 12 አባላትን የያዘ ግብረ ሃይል መቋቋሙ ን ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.