Fana: At a Speed of Life!

በሃረር ለኢድ አልፈጥር በዓል ማክበሪያ ስፍራ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በሀረር ከተማ የ1442ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ማክበሪያ ስፍራ የተለያዩ ሃይማኖት አባቶች የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል ።

የሃረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ፣ የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሰላም አምባሳደሮች ፣ ጸጥታ አካላት እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

በብሄርና በሃይማኖት ሊከፋፍሉን የሚሞክሩ ባዕዳንን ተስፋ የሚያስቆርጥ የአንድነታችን መገለጫ የሆነ ተግባር ነው ብለዋል በጽዳት ዘመቻው ላይ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፡፡

ክልላችን በዩኔስኮ በሰላምና፣ በመቻቻል የተመዘገበችበትን የሀይማኖቶች አንድነትን በማጠናከር እና የጋራ የሆኑ እሴቶቻችን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ የሀረርን ከተማነት ልናስቀጥል ይገባልም ብለዋል ፡፡

በአሁኑ ሰአት አንድነታችንን ለመሸርሸር የሚሰሩ የፀረ-ሰላም ሀይሎች እንዳሉ የገለፁት ርእሰ መስተዳደሩ፤ መላው የክልሉ ነዋሪ ለእነዚህ ሀይሎች ጆሮ ባለመስጠትና አንድነቱንና ፍቅሩን በማጽናት ለክልላችንና ለሀገራችን የወደፊት የልማት ስኬት በጋራ ልንቆምና ልንረባብ ይገባል ብለዋል፡፡

በመሆኑም አገራችን አሁን ካለችበት የለውጥ ጎዳና ወደ ኃላ ሊመልሱ የሚችሉ ሁነቶች እየተስተዋሉ መሆኑን ገልፀው የእነዚህን የፀረ ልማት ሀይሎች ዓላማ በአንድነት ቆመን ልናከሽፈው ይገባል ብለዋል፡፡

የሀይማኖት አባቶቹ አክለውም ሀረር የሰላም የፍቅር የመቻቻል ከተማ መሆኗንና ወደ ቀደመ ማንነቷ ለመመለስና የህዝበ ክርስቲያኑንና የህዝበ ሙስሊሙን ወንድማማችነትና አንድነትን በማጠናከር የሀገራችንን ሰላም ልናስጠብቅ ይገባል ብላዋል፡፡

በተለይም በሀይማኖት መካከል ልዩነት ለመፍጠር ዘወትር ለሚሰሩ ፀረ ሰላም ሀይሎች የዛሬው የጋራ ስራ ተስፋ የሚያስቆርጣቸውና ሀሳባቸውም እንደማይሳካ አመላካች ነው ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.