Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ከቅዳሜ ጀምሮ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጨማሪ ጣቢያዎች ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከቅዳሜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጨማሪ ጣቢያዎች ሊከፍት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ቦርዱ በቀሩት የመራጮች ምዝገባ ቀናት የተሻለ ምዝገባ እንዲካሄድ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ነው ያነሳው፡፡

ከዚህ ቀደም በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ያለውን የመራጮች ምዝገባ ጣቢያዎች እጥረት መኖሩን የገለጸ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታትም የተለያዩ ጥረቶችን እያካሄደ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡

ከስር በተጠቀሱት ዝርዝር አድራሻዎች መራጮች ምዝገባ ማከናውን እንደሚችሉ የገለጸው ቦርዱ ችግሮችን ሪፓርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመር 778 በመደወል ማሳወቅ እንደሚችሉ ነው ያሳሰበው፡፡

ቦርዱ በልዩ ሁኔታ በተለይ በጀሞ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምርጫ ጣቢያዎችን ለመክፈት ለከተማ መስተዳድሩ በተደጋጋሚ ማሳወቁን ገልጾ ወረዳው ቢሮዎችን ማዘጋጀት ባለመቻሉ ከታቀዱት 15 አዳዲስ ጣቢያዎች 6ቱ መከፈት ያለመቻላቸውን ነው ያስታወቀው።

ይህንን ከወረዳው ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት እየሰራ እንደሚገኝም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡

በተለያዩ ኮንዶሚኒየም የተከፈቱ አዲስ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

በየካ አባዶ ኮንዶሚኒየም የተከፈቱ አዲስ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  1. የካ አባዶ ኮንዶሚንየም አርሴማ ብሎክ ምርጫ ጣቢያ 1 (በየካ አባዶ ኮንዶሚንየም አርሴማ ብሎክ ቆርቆሮ ቤት ጊቢ ውስጥ ይገኛል፡፡)
  2. የካ አባዶ መስቀለኛ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 2 ( በየካ አባዶ ኮንዶሚንየም መስቀለኛ መንገድ ላይ ይገኛል፡፡)
  3. የካ አባዶ መቻቻል ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 3 (በየካ አባዶ ኮንዶሚንየም መቻቻል ኮንዶሚንየም ኮሚናል / ቡርቃ ላይ ይገኛል፡፡ )
  4. የካ አባዶ ድልድይ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 4 (በየካ አባዶ ድልድይ ኮንዶሚንየም መግቢያ ላይ ይገኛል፡፡)
  5. የካ አባዶ መስጊድ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 5 (በየካ አባዶ መስጊድ ኮንዶሚንየም ግራር አምባ/ ቆርቆሮ ቤት ጊቢ ውስጥ ይገኛል፡፡)
  6. የካ አባዶ ብርሀን ለአባዶ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 6 (በየካ አባዶ ብርሀን ለአባዶ ኮንዶሚንየም ኮሙናል ውስጥ ይገኛል፡፡)
  7. የካ አባዶ ኮንዶሚንየም ቡርቃ ብሎክ 14 ምርጫ ጣቢያ 7 (የካ አባዶ ኮንዶሚንየም ጂ-7 አካባቢ ውስጥ ይገኛል፡፡

የካ ሃያት ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  1. ሀያት ሀያዎቹ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 1 (ሀያት ሀያዎቹ ኮንዶሚንየም መግቢያ በር ላይ ይገኛል፡፡)

ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  1. አራብሳ ኮንዶሚንየም መተባበር ማህበር ምርጫ ጣቢያ 7 (በመተባበር ማህበር ኮሚውናል ውስጥ ይገኛል ፡፡ )
  2. አራብሳ ኮንዶሚንየም ሰፈረ ሰላም ማህበር ምርጫ ጣቢያ 8 (በሰፈረ ሰላም ማህበር ኮሚውናል ውስጥ ይገኛል ፡፡ )
  3. አራብሳ ኮንዶሚንየም አለም ገነት ማህበር ምርጫ ጣቢያ 10 (አለም ገነት ማህበር ኮሚውናል ውስጥ ይገኛል፡፡ )
  4. አራብሳ ኮንዶሚንየም ፍቅር በአራብሳ ማህበር ምርጫ ጣቢያ 11 (ፍቅር በአራብሳ ማህበር ኮሚውናል ውስጥ ይገኛል ፡፡ )
  5. አራብሳ ኮንዶሚንየም ፍቅር ማህበር ምርጫ ጣቢያ 9 (በፍቅር ማህበር ኮሚውናል ውስጥ ይገኛል ፡፡ )

ጀሞ ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  1. ጀሞ በትግል ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 22 (ጀሞ በትግል ኮንዶሚንየም ጀሞ ሁለገብ የገበያ ማእከል አጠገብ ይገኛል፡፡)
  2. ጀሞ ሰፈረ ሰላም ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 24 (ጀሞ ሰፈረ ሰላም ኮንዶሚንየም አባይ ትምህርት ቤት አካባቢ ይገኛል፡፡)
  3. ጀሞ አሀዱ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 28 (ሴቶች ፌደሬሽን አጠገብ ያለው ኮንዶሚንየም ይገኛል፡፡)
  4. ጀሞ ፍቅር ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 29 (ጀሞ ሁለት ት/ቤት እና አሀዱ መሀል ይገኛል፡፡)
  5. ጀሞ ሁለት ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 30 (ብሩክ ተስፋ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ይገኛል፡፡)
  6. ጀሞ አዲስ አበባ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 31 (ጀሞ አዲስ አበባ ኮንዶሚንየም መንደር 3 ዳዋ ክሊኒክ አጠገብ ይገኛል፡፡)
  7. ጀሞ አዲስ አበባ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 32 (ጀሞ አዲስ አበባ ኮንዶሚንየም ጋር 72 ካሬ ሊዝ መንደር ይገኛል፡፡)
  8. ጀሞ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 33 (ጀሞ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም ጀርባ አባገዳ ሰፈር ወይም ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ ይገኛል፡፡)
  9. ጀሞ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም ምርጫ ጣቢያ 34 (ጀሞ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም ፊት ለፊት ይቻላል መናፈሻ/ ወይም ከመስጊዱ አጠገብ ይገኛል፡፡)

(ጀሞ በተጨማሪ መከፈት የነበረባቸው 6 አዲስ ምርጫ ጣቢያዎች ወረዳው መስተዳድር ቦታ ባለማዘጋጀቱ ምክንያት እስካሁን ሊከፈቱ አልቻሉም።)

ገላን ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  1. ገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 249 ምርጫ ጣቢያ 5 (በገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 249 ከመስኪድ ፊትለፊት ይገኛል፡፡)
  2. ገላን ኮንዶሚንየም ኮሚናል 8 ምርጫ ጣቢያ 6 (ገላን ኮንዶሚንየም ኮሚናል 8 ጤና ጣቢያ ጀርባ ይገኛል፡፡)
  3. ገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 89-93 ምርጫ ጣቢያ 7 (በገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 89-93 ኮሚናል ይገኛል፡፡ )
  4. ገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 135-138 ምርጫ ጣቢያ 8 (በገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 135-138 ኮሚናል ልደታ ፊት ለፊት ይገኛል፡፡ )
  5. ገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 240/14 ምርጫ ጣቢያ 9 (በገላን ኮንዶሚንየም ብሎክ 240/14 ታክሲ ተራ አካባቢ ይገኛል፡፡)

ቱሉ ዶምቱ ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  1. ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 160- 165 ምርጫ ጣቢያ 1 (በቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 160- 165 ኮሚናል ውስጥ ይገኛል፡፡)
  2. ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ፕሮጀክት 12 ምርጫ ጣቢያ 2 (በቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ፕሮጀክት 12 ቁጥር 3 ኮሚናል ውስጥ ይገኛል፡፡)
  3. ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 22-27 ምርጫ ጣቢያ 3 (በቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 22-27 ኮሚናል ውስጥ ይገኛል፡፡ )
  4. ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 268-272 ምርጫ ጣቢያ 4 (በቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 268-272 ኮሚናል ውስጥ ይገኛል፡፡)
  5. ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 306-311 ምርጫ ጣቢያ 5 (በቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ብሎክ 306-311 ኮሚናል ውስጥ ይገኛል፡፡)

ሰሚት ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  1. ሰሚት ኮንዶሚንየም 4ቱ ክዋክብት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር ምርጫ ጣቢያ 01
  2. ሰሚት ኮንዶሚንየም መንበረ ህይወት ማህበር ምርጫ ጣቢያ 02
  3. ሰሚት ኮንዶሚንየም ብሩህ ተስፋ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር ምርጫ ጣቢያ 03

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.