Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የሰብአዊ ዕርዳታ ተደራሽ እንዲሆን መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮ ጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የሚስዮኑ ጊዜያዊ ኃላፊ ፊሊፕ ቦቨርዲን ትናት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

አቶ ደመቀ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ድርጅት፤ በኢትዮጵያ በሚፈጠሩ ሰው ሰራሽ ግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ግንባር ቀዳም በመሆን እያበረከተ ስላለው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሚስዮኑ ኃላፊ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ ለማስከሄድ የበጀት ጭማሪ ለማድረግ ዕቅድ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ እስረኞችንና ተፈናቃዮች መጎብኘታቸውን ለአቶ ደመቀ አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም ከቤንሻንጉል፣ ከትግራይ እና ከኦሮሚያ ክልሎች ተፈናቅለው ፤በአገሪቱ በተለያየ ስፍራ የሚገኙ እርዳታ ፈላጊዎችንም እየረዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የስራ ሃላፊው ቀይ መስቀል እስከአሁን በትግራይ ክልል ያከናወናቸው ተግባራት ላይ ደስተኛ መሆናቸው ጠቅሰው ፤ እርምት የሚፈልጉ ጉዳዮችን አቅርበዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሰብአዊ ዕርዳታ ተደራሽ እንዲሆን መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ያስገንዘቡት
አቶ ደመቀ ፥በሁለተኛ ዙር ለ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ መደረጉን እና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እርምጃዎች ይወሰዳል ነው ያሏቸው፡፡

የፀጥታ ስጋት ባሉባቸው ውስን ቦታዎች ጭምር መከላከያ ከሲቪል ጋር በመቀናጀት ድጋፍ እየተሰጠ ነው ሲሉ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.