Fana: At a Speed of Life!

የአርባ ምንጭ ድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርባ ምንጭ ከተማ በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ግንባታቸው ከተጠናቀቁ ስድስት ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች መካከል የአርባ ምንጭ ድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በተገኙበት ተመርቋል።

በዛሬው እለት በከተማው ግንባታቸው ከተጠናቀቁ 6 ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የአርባምንጭ ድልፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከእነ ሙሉ የህክምና መሳሪያዎች 16 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የፈጀ መሆኑን ከከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንዲሁም በዘጠኝ ሚሊየን ብር የተገነባው የአርባ ምንጭ ከተማ ህዝብ መዝናኛ ፓርክ፣ በ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የተገባው የጉርባ ወጣቶች  ማዕከል፣ በ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በቤሬ ዕድገት በር ቀበሌ የተገነባው የእንስሳት ክሊኒክ ማዕከል፣ በጉርባ ቀበሌ በ12 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎ የተገነባው የህዝብ መሸጋገሪያ ድልድይ ተመርቀዋል::

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፌ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ፣ የደቡብ ክልል ብልጽግና  ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እና በየደረጃው የሚገኙ የዞንና የከተማው አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.