Fana: At a Speed of Life!

ከጁንታው ሃይል መካከል ማይካድራ ላይ ጭፍጨፋ በማድረግ ወደ ሱዳን የሄደው ሃይል ወደ ሁመራ ሊገባ ሲል ተደመሰሰ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከጁንታው ሃይል መካከል ማይካድራ ላይ ጭፍጨፋ በማድረግ ወደ ሱዳን የሄደው ሃይል ወደ ሁመራ ሊገባ ሲል መደምሰሱን የመከላከያ ሚኒስትር የሃይል ስምሪት ሃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገለፁ።

ለወራት አሜሪካና ሱዳን ከሚገኙ የጁንታው አባላት ድጋፍ እየተደረገለት ስልጠና ሲወስድ የነበረው ሃይል በተደጋጋሚ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጅ ይህ ሙከራቸው በተደጋጋሚ በመከላከያ ሰራዊቱ ሲከሽፍ ቆይቷልም ነው ያሉት።

ከተደጋጋሚ ሙከራ በኋላም 320 ከጁንታው ሃይል በሃምዳይት ሁመራ በኩል ትጥቅና የተለያዩ መድሃኒቶችን ይዞ ሊገባ ሲል ገሚሱ በመከላከያ ሰራዊቱ ሲደመሰስ ገሚሱ መማረኩንም ተናግረዋል።

አሁንም ከኋላ የቀረ ሃይል መኖሩን የገለጹት ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋዬ መከላከያ ሰራዊቱ አሁንም ይህንን ሃይል ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በሰጡት መግለጫ ሀገራዊ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው በአሜሪካ ይገኙ የነበሩና ሀገርን በመካድ ሱዳን ካርቱም ከሚገኙ የጁንታው አመራሮች ጋር ወደ ሀገር ውስጥ የመገናኛ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ የነበሩትም በሰራዊቱ ተደምስሰዋል ብለዋል።

ብዛት ያለው የሬዲዮ መገናኛ ፣ ሳተላይት ስልኮችና የተለያዩ መድሀኒቶች መያዛቸውንም ነው የገለጹት።

ጁንታው በተከፋይ አክቲቪስቶቹ የሚረጨው የውሸት ዜና ብቻ በመሆኑ ህብረተሰቡም ይህን እንዲገነዘብ ጥሪ አቅርበዋል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.