Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 10 ወራት ከማዕድን ዘርፍ 513 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ  ባለፉት ወራት በተለያዩ መንገዶች   ማሻሻያና ማስተካከያ እየተደረገለት መሆኑ ተገለፀ፡፡

በዚህም ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ አቅምን የማሳደጊያ ተግባራትም መከናወናቸውን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ወራት ለውጭ ገበያ አቅርባ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ካገኘችባቸው ምርቶች መካከል የማዕድኑ ዘርፍ በተለይም ከወርቅ የተገኘው ገቢ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል።

ባለፉት 10 ወራት 5 ሺህ 921 ነጥብ 52 ኪሎ ግራም የማዕድን ምርት ለውጭ ለማቅረብ ታቅዶ 6 ሺህ 785 ነጥብ 42 ኪሎ ግራም ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ነው ያሉት።

በገቢ ደረጃም ከዘርፉ 501 ነጥብ 73 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 513 ሚሊየን ዶላር ማግኘት መቻሉንም ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህ ውስጥ 504 ነጥብ 73 ሚሊየን ዶላሩ ከወርቅ ምርት የተገኘ ሲሆን ሚኒስቴሩም በባህላዊ መንገድ ማዕድን አምራቾችን አቅማቸውን አሳድገውና በኢንዱስትሪ ታግዘው እንዲያለሙ ለማድረግ እንደሚሰራም ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በዘርፉ ለማልማት ፈቃድ ወስደው ወደስራ መግባት ያልቻሉ ፣ ስራውን በተጓተተ መልኩ ያከናወኑ እና ቃል የገቡትን በተገቢው ለውጤት ያላበቁ 63 ተቋማት ፈቃዳቸው መሰረዙን ጠቁመዋል።

በተያያዘም በዘርፉ ለመሰማራት ፈቃድ ወስደው እና ውል አስረው ወደስራ ያልገቡ 27 የማዕድን አውጪ ተቋማት ከዛሬ ጀምሮ ፈቃዳቸው መሰረዙንም በመግለጫው አንስተዋል።

በይስማው አደራውወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.