Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባን የኢትዮጵያ የባህል ማዕከል እናደርጋታለን- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ የፊቼ-ጨምበላላ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሯል::
በኢትዮጵያ ያሉ በርካታ የብሔር ብሄረሰቦችን ቱባ ባህሎችን በመጠበቅ እና ለቱሪዝም ዘርፍ ማዋል ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን የኢትዮጵያ የባህል ማዕከል ለማድረግ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩም አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከተማነት በተግባር ለማረጋገጥ ለሲዳማ ባህል ማዕከል መገንቢያ የሚሆን ቦታ ማዘጋጀቱን ወ/ሮ አዳነች የገለፁት።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ ከመስጠት በተጨማሪ የፊቼ-ጨምበላላ በዓል በከተማዋ እንዲከበር ላደረገው ድጋፍ በከልሉ ስም ምስጋና አቅርበዋል ።
የባሕልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው በመርሐግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጨምባላላ ባሕላዊ ይዘቱንና ታሪካዊ ሁነቱን በጠበቀ መልኩ ለትውልድ እንዲተላለፍ የመስኩ ሙሁራን እና የሚመለከታቸው አካላት የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በሚያሳድግ መልኩ በትብብር ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን ከከተማ ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
“ፊቼ-ጨምበላላ ” የሰላም ፣የመከባበር፣የፍቅር ፣የአብሮነት ፣የመቻቻል እና የእርቅ ተምሳሌት በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.