Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ኢምባሲ ለአማራ ክልል የህክምና መሣሪያዎችን ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ ) የቻይና ኢምባሲ ከቻይና ኢኮኖሚና የንግድ ማእከል ጋር በመተባበር 23 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና መሣሪያዎችን ለአማራ ክልል ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ 255 ሺህ 300 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 20 ቬንትሌተር፣ 8 ከፍተኛ የልብ ህክምና መስጫ መሣሪያዎች እና አንድ የህመምተኞችን ሁኔታ የሚከታተል መሣሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እርዳታውን ያስረከቡት በቻይና ኤምባሲ አማካሪ ሊው ዩ የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ ቻይና ድጋፏን ስታደርግ ቆይታለች ብለዋል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የወንድማማችነት እና የቤተሰባዊ ድጋፍ መሆኑን እንረዳለን፤ በዚሀ ወረርሽኝ ዓለም መተጋገዝ እንዳለበት የሚያሳይ ሲሆን ድጋፉም ለህክምና ተቋማት ይከፋፈላል ብለዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ ቻይና በክልሉ ያላትን ኢንቨስትመንት እንድታጠናክር መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.