Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ።

የፓርኩ የመጀመርያ ምዕራፍ ግንባታ በ50 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በውስጡ 5 ሺህ 500 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ስምንት የማምረቻ ህንፃዎችን ይዟል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ለማምረቻ ኢንዱስትሪ አስፈላጊ የሆኑ የመሰረተ ልማቶች እየተሟላለት ነው።

ፓርኩ ሀገሪቱ እየተገለገለችበት ከምትገኘው የጁቡቲ ወደብ እና ሌሎች በአቅራቢያ ለሚገኙ ወደቦች በቅርብ ርቀት መገኘቱ በወጪ ንግድ ዘርፍ ለሚሰማሩ አምራቾች ሳቢ ያደርገዋል፡፡

በአላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.