Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር 11 የንግድ ስምምነቶችን ተፈራረመች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር 11 የንግድ ስምምነቶች መፈራረሟን አስታወቀች።

የንግድ ስምምነቱ 7 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ዋጋ እንዳለው ተገልጿል።

የብሪታንያ የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ ያለውን ተሳትፎ ማሳደግን አላማው ያደረገ በእንግሊዝ የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ በአፍሪካ አዲስ የልማት አጋርነትን መተግበር የሚያስችል እቅድ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

እቅዱ በአብዛኛው በመሰረተ ልማት እና በንግድ ላይ ያተኮረ ይሆናል ነው የተባለው።

ብሪታንያ በአፍሪካ ለእርዳታ የምትለግሰውን ገንዘብ ለልማት ማዋልና በተለይም የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አዲሱ የልማት አጋርነት አካል ይሆናል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅትም በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በታዳሽ ሃይል እና በሴት ስራ ፈጣሪዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ገልጿል።

በአህጉሪቱ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገቡ ያሉ ሃገራት መበራከትና ያለው የሰው ሃይል የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን አስችሏታል ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.