Fana: At a Speed of Life!

በኮምቦልቻ እና በሀዋሳ የተገነቡ አየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማዎች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሀዋሳ እና ኮምቦልቻ ያስገነባቸውን አየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማዎች አስመረቀ።

ባለስልጣኑ በሀዋሳ ኤርፖርት ያስገነባውን የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን የኮምቦልቻው ደግሞ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓበታል።

በሀዋሳ የተገነባው ማማ ሲመረቅ በቦታው የተገኙት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተወካይና በአቪዬሽኑ የሬጉሌሽን ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀና ተገኘወርቅ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪየሽን ድርጅትን ኮንቬንሽን ከፈረሙ በዓለም ከሚገኙ ጥቂት ሀገሮች ውስጥ ቀደምት መሆኗን ገልፀዋል።

የሀገሪቱን የአየር ክልል ደህንነት ይበልጥ አስተማማኝ ለማድረግና የአየር ትራንስፖርቱን አድማስ ለማስፋትም መንግስት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በመመደብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ የግንባታ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ነዉ የገለጹት።

የሀዋሳ ኤርፖርት ሥራ አሥኪያጅ አቶ ገብረ ሚካኤል ብርሃኔ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በየኤርፖርቶቹ የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማዎችን በመገንባት ዓለም አቀፍ ልኬትን ለማሟላት በየጊዜው አገልግሎት አሰጣጡን እያቀላጠፈ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ በኮምቦልቻ የተገነባው የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማ የተገኙት፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተወካይ እና ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ፍቃዱ ውለታዉ  የኮምቦልቻ አየር መቆጣጠሪያ ታወር ለሀገሪቱና ለክልሉ ኢኮኖሚ ያዊ እንቅስቃሴ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።

እሸቱ ወ/ሚካኤልና ታምራት ቢሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.