Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በጋዛ የአልጀዚራና አሶሼትድ ፕሬስ ቢሮዎች የሚገኙበትን ህንፃ አወደመች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በጋዛ የአልጀዚራና አሶሼትድ ፕሬስ ቢሮዎች የሚገኙበትን ህንፃ በአየር ጥቃት አወደመች።

የህንፃው ባለቤት ከእስራኤል የደህንነት መስሪያ ቤት በህንፃው ላይ ጥቃት ሊፈፀም መሆኑን መረጃው ከደረሰው በኋላ ሰዎች ህንፃውን እንዲለቁ አድርጓል።

ህንፃው በርካታ መኖሪያ ቤቶችን እና ቢሮዎችን የያዘ ነበር።

የእስራኤል ጦር ህንፃው ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ወታደራዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ሰዎች ቤት እንደነበር አስታውቋል።

አልጀዚራም ህንፃው ሙሉ በሙሉ ሲወድም በቀጥታ ስርጭት እንዳስተላለፈው ቢቢሲ ዘግቧል።

አሶሼትድ ፕሬስ ባወጣው መግለጫ ፤ የእስራኤል ጦር በህንፃው ላይ የወሰደው እርምጃ አስፈሪ ነው ብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.