Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በአፍሪካ ህብረት የሚካሄድውን የሦስቱ አገራት ድርድር እንደምትደግፍ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ቻይና በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት ግድቡን በተመለከተ የሚካሄደውን የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለፃለች።
በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል የልዑክ ኃላፊ ዢ ቲያን እንደተናገሩት ግድቡ የዓለም አቀፉን ህብረተሰብ ቀልብ የሳበ ነው።
ለአብነትም በመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ጉዳዩ መነሳቱን አስታውሰዋል።
ቻይና እንደአንድ የአፍሪካ ወዳጅ አገር ግድቡ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ትረዳለች ብለዋል።
በመሆኑም በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት ግድቡን በተመለከተ የሚካሄደውን የሦስትዮሽ ድርድር ቻይና እንደምትግፍ ገልጸዋል።
ቻይና የአፍሪካ አገራት ወዳጅ እንደመሆኗ ግድቡ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው እንረዳለን፤ በተለይም ደግሞ ለኢትዮጵያ ልማት ያለውን ጠቀሜታ እናውቃለን” ብለዋል።
ይህንንም ተከትሎ ቻይና በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት ግድቡን በተመለከተ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ሦስቱ አገራት የሚያካሂዱትን ድርድር ትደግፋለች ብለዋል።
“አፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት ግድቡን በተመለከተ የሚካሄደውን ድርድር እንደግፋለን፤ በውይይት መፍትሄ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት ትክክለኛ መንገድ ነው፤ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርህም እንደግፋለን” በማለት ተናግረዋል።
ቻይና ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የአፍሪካ ህብረት ከሚያካሂደው ድርድር እንዳይወጡና ልዩነቱም በውይይት እንዲፈታ ታበረታታለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.