Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ግለሰብ ቤት በተደረገ ፍተሻ 112 ሺህ ሃሰተኛ የብር ኖት ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በፃግብጂ ወረዳ በአንድ ግለሰብ ቤት በተካሄደ ፍተሻ 110 ሺህ ባለ ሁለት መቶ ብር እና 2ሺህ ባለ መቶ ብር በድምሩ 112 ሺህ ሃሰተኛ የብር ኖት መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ።

የወረዳው ፓሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ አለሙ እንደገለፁት፥ ሃሰተኛ የብር ኖቱ የተገኘው በወረዳው 02 ቀበሌ በለቃ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነዋሪ ከሆነ አንድ ግለሰብ ቤት ነው።

በቀበሌው ህገ ወጥ ድርጊት ለመፈፀም የተዘጋጀ ግለሰብ እንዳለ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት የፀጥታ አካሉ ባደረገው ፍተሻ የሃሰተኛ የብር ኖቱ መገኘቱን ተናግረዋል።
ከሃሰተኛ የብር ኖቱ በተጨማሪ አንድ ሽጉጥ መገኘቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተጠርጣሪው ለጊዜው በመሰወሩ ፖሊስ ክትትል እያደረገበት መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.