Fana: At a Speed of Life!

ከ69 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም 69 ሚሊየን 215 ሺህ 956 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለፀ፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ እና ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን ወደ ሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች 66ሚሊየን 744 ሺህ 994 ግምታዊ ዋጋ ሲኖራቸው ሊወጡ ሲሉ የተያዙት ደግሞ 2ሚሊየን 470 ሺህ 962 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ናቸው ተብሏል፡፡
አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሀዋሳ፣ ጅጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌ፣ ባህርዳር፣ ጋላፊ፣ አዲስ አበባ ቃሊቲ፣ ጅማ፣ አዳማ፣ አዋሽ፣ ኮምቦልቻና አሶሳ ደግሞ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ የተያዙበት የጉምሩክ ቅርንጫፎች ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ኤርፖርት፣ በሞያሌ እና በድሬዳዋ ከፍተኛ የገቢ ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የታየ ሲሆን 41 ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ጭነው መያዛቸውን ታውቋል፡፡
ኮንትሮባንድ እቃዎቹ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ምግብ ነክ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅና ጫማ፣ መለዋወጫ፣ መድሀኒትና አደንዛዥ ዕፅ፣ የጦር መሳሪያዎች እና ሌሎችንም ያጠቃለሉ መሆናቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.