Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ባለፋት ስድስት ዓመታት ከ23 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ባለፋት ስድስት ዓመታት ከ23 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ያከናወናቸውን የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተበት 2007 ዓ.ም አንስቶ እስከ ዛሬ ያከናወነውን የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር አገልግሎት ስራዎችን አቅርቦ በአጋር አካላት ያስገመግማል፡፡

ባለፋት ስድስት አመታት 112 የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የተሰጡ ሲሆን፤ ከ23 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡

አዳማ፣ ኦዳ ቡልቱ እና መደወላቡ ዩኒቨርሲቲዎች የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራ ተሞክሯቸውን ያቀርባሉም ነው የተባለው፡፡

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ምክክር በዘርፉ ስትራቴጂና ዕቅድ የማውጣት ሀሳብ ይገኝበታል፡፡

በኤርሚያስ ቦጋለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.