Fana: At a Speed of Life!

ምሁራን የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ እንደሚመነጭ ለአለም ማስረዳት ይኖርባቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ምሁራን የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ እንደሚመነጭ ለአለም ማስረዳት እንደሚኖርባቸው ተገለጸ።

‘‘የዩኒቨርሲቲዎች ትብብር ለሰላማዊና ፍትሃዊ የአባይ ወንዝ ተጠቃሚነት’’ በሚል ርዕሰ የታላቁ ህዳሴ ግድብ እና የዩኒቨርስቲዎች ሚና ላይ ያተኮረ ዉይይት በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

ውይይቱን የከፈቱት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ፤ ግብፅ በተዛባ ትርክት ፍትሃዊ ባልሆነ የቅኝ ግዛት ስምምነቶች በመነሳት ወንዙን እኔ ብቻ ልጠቀም የሚል ሃሳብ ትክክል አይደለም ።

ምሁራን እና የዘርፉ ተመራማሪዎች ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሃብቷን የመጠቀም መብቷን ለህብረተሰቡ እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስረዳት እንዳለባቸውም ነው የጠቆሙት፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ዶክተር ኢንጂነር ይልማ ስለሺ፤ ‘‘ግብፅ እና ሱዳን ውሃ የለንም’’ የሚል የተሳሳተ ሃሳብ ለአለም እያቀረቡ ቢሆንም ግብፅ 154 ትሪሊየን የከርሰ ምድር ዉሃ እንዳላት ኢትዮጵያውያን ምሁራን ይህንን ለአለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ማሳወቅ አለባቸው ብለዋል ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ግድቡ 80በመቶ መድረሱን እንዲሁም ዘንድሮ ሁለት ተርባይን ተጠቅመን ሀይል እናመነጫለን ማለታቸው ተነስቷል።

በመድረኩ ‘‘ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለው ጠቀሜታ እና የምሁራን ሚና ምን መሆን አለበት’’ በሚል ርሰ ጉዳይ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል ።

በውይይቱ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን እየተሳተፉ ነው ።

በአልማዝ መኮነን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.