Fana: At a Speed of Life!

ህንድ በከባድ አውሎ ንፋስ ልትመታ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ19 ወረርሽኝ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰባት ህንድ አሁን ደግሞ ከባድ ንፋስ አዘል ዝናብ ሊመታት መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በምእራባዊ የህንድ ግዛት ሊያጋጥም ይችላል ለተባለው አደጋ የሃገሪቱ መንግስት ከወዲሁ መዘጋጀት ጀምሯል ነው የተባለው፡፡

ይህ አይነት ከባድ ተፈጥሯዊ ክስተት በህንድ ካጋጠመ 23 አመታት መቆጠሩን ነው የቢቢሲ ዘገባ ያመለከተው፡፡

ታኡክታኢ የተባለው ከባድ ንፋስ አዘል ዝናብ ከወዲሁ በምእራባዊ የሃገሪቱ ግዛት ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ለስድስት ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአደጋው ሳቢያ ባህር ላይ የቀሩና ከ400 በላይ ሰዎችን የጫኑ ጀልባዎችን በማፈላለግ የነብስ አድን ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

ህንድን የመታት ታኡክታኢ የተባለው ከባድ ንፋስ አዘል ዝናብ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ባደቀቀው የሃገሪቱ የጤና ዘርፍና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ተጨማሪ ጫናን እንዳይፈጥር ተሰግቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.