Fana: At a Speed of Life!

ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር ጠመዝማዛ መንገዶችን ማለፍ የሚጠይቅ ዕድል እና እዳን አጣምሮ የያዘ ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር ጠመዝማዛ መንገዶችን ማለፍ የሚጠይቅ ዕድል እና እዳን አጣምሮ የያዘ መሆኑን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከግንቦት 9 እስከ ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ሃገራዊ የምክክር መድረክ የማስጀመሪያ መርሃግብር ዛሬ ተካሄዷል፡፡

ሚኒስትሯ ለውጡን ተከትሎ ዴሞክራሲ ፣ ሰላምና ፍትህን በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት እንዲቻል ተቋማዊ ምሰሶዎችን የማቆም እና የመገንባት ተግባራት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ሃገር በተወሰነ አካል አቋም እና ፍላጎት ማቆም ስለማይችል የሁሉንም ተሳትፎ ያካተቱ መድረኮችን በማከናወን ዘላቂ ሰላምን እውን ለማድረግ የሚረዳ ጉዞን ለመገምገም መድረኮቹ አጋዥ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሽግግር ሂደት፣ ብሄራዊ መግባባት፣ምርጫ 2013 እና ከዚያ ባሻገር የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል ተብሏል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የምክር ቤት አባላት፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ምሁራን ተገኝተዋል።

በቀጣይ በመድረኮቹ ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ምሁራን ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች ፣ የሲቪክ ማህበራት እና ሌሎች አካላት በተጠቀሱት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንደሚይዙ ይጠበቃል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.